Discover
ባህልና ወጣቶች | Deutsche Welle

2736 Episodes
Reverse
ከ30 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጉልህ ተሳትፎ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ዛሬም አልታከቱም። እሳቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማምጣት የተሻለ መንገድ ነው ያሉትን የትግል ስልት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለማስረዳት ይጥራሉ። መርኀቸው በሌሎች በርካታ ሃገራት ውጤት አስገኝቷል የሚሉት ሰላማዊ ትግል ነው።
በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን ላረ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩ መካከል ሰባት ሺህ የሚደርሱ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸው የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው ትናንት ወደ ሐርጌሳ ተመልሷል። ይህን ጉብኝት በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም።
ሰሞኑን በፋኖ ኃይሎች እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ውጊያ መኖሩ ተገለጠ ። በውጊያው የፋኖ ኃይሎች ተጨማሪ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውም ተገልጧል ። የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ «ጽንፈኛ» ሲሉ የገለጡት ኃይል ትንኮሳ ከመፈጸም ውጪ በየቦታው የመዋጋት አቅም የለውም ብለዋል ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ወጣቶች የተለያዩ ቀናቶችን ሲያከብሩ ይስተዋላል ፡፡ ለዚህም ገንዘብ ያሰባስባሉ።
በተማሪዎች ዘንድ ስለሚከበሩት እነዚሁ ቀናት ጠቀሜታ እና ጉዳቶች ላይ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አቅራቢ ትንቢት ሰውነት ከሁለት ሴት ታዳጊዎች ጋር ተወያይታለች።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፤ኢሰመኮ የመዘዋወር ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል ሲል ያወጣው መግለጫ እና የመንግሥት ምላሽ፣ ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ሽግግርን እንዲሁም የኢትዮጵያ የኒዩክሌር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት፦ የማኅብራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት ዝግጅት ።
በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በድጋፍ እጥረት ችግር ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው ። ደ ቀዬያቸውና ነባሩ ኑሯቸው እንዳልተመለሱም ተገልጧል ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች በሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ አማራጭ የፖለቲካ ሐሳባቸውን ለማቅረብ መቸገራቸውን የዐሥራ አንድ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው ሰላም ጥምረት አመለከተ፡፡
የባህል ሙዚቃን ከነሙሉ ክዋኔ እና ባህላዊ አልባሳትን ቱባውን ባህል ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የጎላ ሚና የተጫወተው የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን በ1960ዎቹ አጋማሽ ነበር፡፡
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትግራይ ኃይሎች አባላት ሰሞኑን የጀመሩትን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል እንዲቀላቀል ጥሪ ጠየቁ ። ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት ዴሞክራሲ የቆየ የትግራይ ሕዝብ የለውጥ ፍላጎት ወደ ጎዳናዎች መፍሰስ ጀምሯል ብሏል ። የትግራይ ኃይሎች ባለፈው ሰኞ የጀመሩት ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል ።
በተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሁሉን አቀፍ ልማትና መረጋጋትን በማስፈን «የስደትና መፈናቀል ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል» ያለውን ፍኖተ ካርታ ዛሬ ይፋ አደረገ ።
ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችም የአሥመራና የአዲስ አበባን መሪዎች በመደገፍ ጠቡን እያባባሱት መሆናቸዉ እየተነገረ ነዉ።የአፍሪቃና የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጉዳይ የፖለቲካ ተንታኝ አብዱረሕማን ሰይድ እንደሚሉት የአዲስ አበባና የአሥመራ መሪዎች ባሕሪም ልዩነቶችን በድርድር ለማስወገድ የሚመች አይመስልም
የዘንድሮው የኖቬል ሽልማት በኬሚስትሪ ዘርፍ ተፈጥሯዊ የብረት ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ምርምር ላደረጉት ሶስት ሳይንቲስቶች ተሰጥቷል።ይህ ግኝት ብክለትን ለመቀነስ፤በረሃማ በሆኑ አካባቢዎች እርጥበታማ አየርን በመጭመቅ ዝናብ እንዲኖር ለማድረግ፣ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።በፊዚክስ ዘርፍ ደግሞ የኳንተም ሜካኒካል መተላፊያ አሸናፊ ግኝት ሆኗል።
ዛሬ ጠዋት ጀምሮ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የሚገኙ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሞኾኒ መንገድ በመዝጋት ወደ አላማጣና ወደ መቐለ የሚደረግ የተሽከርካሪዎች ጉዞ አስተጓጉለው የዋሉ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ትላንት ሙሉቀን ተዘግተው የዋሉ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት፣ ውቅሮ እና አጉላዕ ከተሞች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች ዛሬም ተዘግተው አርፍደዋል
በመተከል ዞን የድባጢ ወረዳ ገጠራማ ቦታዎች እና ቡሌን ወረዳ ጎንጎ አካባቢዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እክል እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ባለፈዉ ቅዳሜ ጠዋት በድባጢ ወረዳ በርበር በተባለ ቀበሌ የቀበሌው አስተዳደር ቢሮ ተቃጥሎ ማየታቸውን ያነጋገርናቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ አመልክተዋል
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ታህሳስ 22 ቀን 2016 በአንድ ወር ውስጥ ይፈፀማል የተባለና ለኢትዮጵያ የባህር በር ያስገኛል የተባለለት በ"ሰበር ዜናነት" የተገለፀ የመግባቢያ ስምምነት ቢፈራረሙም ጉዳዩ ከሶማሊያ፣ ግብጽ የአረብ ሊግ እና ሌሎችም ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞት ተግባራዊ ሳይሆን ሁለት ዓመት ሊሞላው ሁለት ወራት ቀርተውታል።
እውቅና የተሰጣቸው እነዚህ ተሸላሚዎች፣ በየተሰማሩበት ሙያ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉ መሆናቸውን፣የኖቫ ኮኔክሽን ዳይረክተር ዶክተር ጋሻው አብዛ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ወዲህ ባካሔዳቸው ጨረታዎች ከ690 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለባንኮች አከፋፍሏል። ጨረታዎቹ በትይዩ ገበያ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የውጪ ምንዛሪ ገበያውን ማረጋጋት ቢችሉም ዋንኛ ዓላማቸውን ያሳኩ አይመስልም። በመደበኛ እና ትይዩ ገበያዎች የምንዛሪ ተመን ሲጨምር ልዩነታቸው አልጠበበም።
ዛሬ ከመቐለ ዓዲግራት የሚወስደውን ጎዳና የዘጉ የትግራይ ኃይሎች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ጎዳናው እንደዘጉ ነበሩ። ትላንት የግዚያዊ አስተዳደሩፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ የህወሓት ሊ/መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የሠራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች ከተቃዋሚዎቹ የሠራዊት አባላት ጋር ስላካሄዱት ዝግ ስብሰባየተባለ ነገር የለም።
የቀደመው የጀርመን መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የውጭ የሰው ኃይልን ለመሳብ አልሞ ነበር ፈጣኑን የዜግነት አሰጣጥ ሕግ ከአንድ ዓመት በፊት ያወጣው። ሕጉ ከወግ አጥባቂዎቹ ቡድን ጠንካራ ተቃውሞ ከተነሳበት በኋላ ሲሰረዝ የውጭ ዜጎች የጀርመን ዜግነት ለማግኘት ጀርመን መኖር ያለባቸው አነስተኛው ጊዜ ወደ አምስት ዓመት ከፍ ብሏል።